ክረምት ሲገባ ቦቆሎ እና ስኳር ድንች በየመንገዱ ማየት የተለመደ ነወ፡፡ በተለይ ስኳር ድንች በጣም ብዙ አይነት አሰራር ቢኖረውም እኛ ሀገር ግን ልክ እንደ ድንች ተቀቅሎ ሲበላ ብቻ ነው ብዙ ጊዜ የምናየው፡፡ የስኳር ድንች ወጥ በቀላሉ እንዴት እንደምንሰራ እናያለን
ግብአት
- ድንች ስኳር - ተቀቅሎ የተከተፈ
- 2 ሽንኩርት- የተከተፈ
- 1 ቲማቲም - የተከተፈ
- 2 ፍንክት ነጭ ሽንኩርት - የተከተፈ
- የቲማቱም ፔስት - ታሽጎ የሚሸጠው የተፈጨ ቲማቲም
- ከሪ ፓውደር
- ክኖር
- ቃሪያ
- ቅቤ
- 1 እንቁላል
አሰራር
- መጥሻ ላይ ዘይት መጋል
- ነጭ ሽንኩርት ጨምሮ ቀላ እስኪል መጥበስ
- ሽንኩርት መጨመር - ማቁላላት
- ቲማቲም መጨመር
- የቲማቲም ፔስቱን መጨመር
- ቃርያ መጨመር
- ቅመሞቹን መጨመር
- ውሀ ጠብ አድርጎ ማቁላለት
- ድንች ስኳሩን መጨመር
- ውሀ ጠብ እያረጉ እብሮ ማብሰል
- በደምብ ከተዋሀደ በኋላ 1 እንቁላል መሀል ላይ መስበር
- እንቁላሉ ሲበስል ለገበታ ማቅረብ
- ከዳቦ ጋር ቢቀርብ ይመረጣል
